ታዝባችሁ ከሆነ በዘመናዊ የተሰጥኦ ውድድሮች (Got Talents) ሳይቀር በውትድርና ያገለገሉ ወይም እያገለገሉ ያሉ ወታደሮች ለውድድር ሲቀርቡ የውድድሩ ዳኞች ከሁሉም ነገር በፊት ለአገልግሎታችሁ እናመሰግናለን ነው የሚሉት።ይህ ለመስዋእትነታቸው የሚከፈላቸው የክብር ዋጋ ነው።
እኛ ጋርም ነበረ።
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በፓርላማ ውሏቸው ወታደር ለመመልመል ተቸግረው እንደነበር በማዘን ጭምር ገልጸዋል። በእርግጥ አሳዛኝ ነው። ምክንያቶቹ ጥናት ቢያስፈልጋቸውም እኔ በግሌ የሚታየኝ ነገር አለ። ወታደር ለመሆን ወይ ክብር ወይ ጥሩ የሞያ አማራጭ( ከጥሩ ክፍያ ጋር) ካለበለዚያ ደግሞ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ የተረዳና ሊታደጋት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆነ መሆን አለበት።
ሶስተኛውን ለጊዜው እንተወውና ሁለቱ አማራጮች በእርግጥ በተቋሞቻችን ውስጥ ነበሩ ወይ? እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ወይም ግለሰብ በዙሪያው የሚያውቀው አንድ ወታደር ወይም ፖሊስ አለ። በተቋሙ ያላቸውን ቦታና ማህበረሰቡ የሚሰጣቸውን ክብር እያወቀ እንዴትስ ይህ ትውልድ ውትድርናን የሂወት አማራጩ እንዲያደርግ ይጠበቃል።
በአንድ ወቅት የገጠመኝን ላካፍላችሁ። ለሰራ ጉዳይ ወደ አንዱ የሀገራችን ከፍል ስንጓዝ በአንድ አካባቢ ሽፍቶች እንደሚያስቸግሩና ለደህንነታችን እንደሚያሰጋን ተነገረን ። የነበረን አማራጭ በአካባቢው ወደሚገኝ የፖሊስ ማዘጃ ሄደን ጥበቃ እንዲደረግልን መጠየቅ ነበር። ፖሊስ የሰጠን መልስ ከማህበረሰቡም የተደገመልን ምክር ያለፖሊስ በራሳችን ብንሄድ የተሻለ እንደሚሆን ነበር። ፖሊስ ካለ እንዲያውም ተጋላጭ እንደምንሆን ነበር። ምርጫም ስላልነበረን እንደተባልነው አደረግን።
ከተሞች አካባቢም ተዘርፋችሁ ወይም ድብደባ ደርሶባችሁ ፖሊሰ ጣቢያ ስትሄዱ ለመርዳት አይደለም ቃላችሁን ለመቀበልም ብዙ ፍላጎት የለም። አይገርማቸውምም።
ይህ የአሁኑ ክስተት ሁላችንም ምን ያህል የእያንዳንዳችን ሂወት በአንድ ወታደር ወይም ፖሊስ ሂወት ላይ የቆመ እንደሆነ ያየንበት ወቅት ነው። ሁኔታወችን ለማስተካከል እንደ ሀገር ጥሩ አጋጣሚ ይመስለኛል። የዜጎች ድጋፍ የሚያበረታታ ነው። ነገር ግን ተቋማዊ መሆን ይኖርበታል። እንደ ህዝብ የምናገኘው እንደ ህዝብ የሰጠነውን ነው። ለዚህም አላማ የሚቆም ኢትዮጵያዊ ይጠፋል የሚል እምነት በፍጹም የለኝም። ያ እንዲሆን ተቋሞቹንም አብረን መፈተሽ እንደሚኖርበን አስባለሁ።
አይገርማችሁም። እረፍት ላይ ያሉ ለዛውም ከመከላከያ ስራ ለብዙ ጊዜ ውጭ ሆነው በአጋጣሚና ያለበቂ ዝግጂት ጦር ሜዳ ሄደው ብንሞት እንመርጣለን ብለው እንደገና ወታደር የሆኑ ጀግኖች። ይሄን ይታደሉታል እንጂ አይማሩትም። በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያላቸውን ሀብት መጠቀማቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። ወታደር እንደዚህ ነው።
Showing Up ^ Exposure Matters!! It Is the First Key Step Leading You Where You Want to Go
Be bold to embrace It!
Comments