የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ
ጊዜ ተጓዥ ነው። እድሜም እንዲሁ። አሁን ላይ ድሮ በሚባል ደረጃ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያለን በት/ቤታችን የሀገራችን ብሄራዊ መዝሙር ከልብ እንዘምር ነበር። የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ እንደ እኔ ልጅ (እንደተንኮለኞች ደግሞ አጭር) ስለነበርኩ ከፊት ስለምሰለፍ ብዙ ጊዜ ባንድራ የመስቀል እድል ነበረኝ። አለማየሁ(ሌላኛው አጭር) ካልቀደመኝ በስተቀር። ባንዲራ ሲወጣና ሲወርድ ልክ እንደ ቅዳሴ መጀመሪያ ሁሉም ባለበት ነበር የሚቆመው።
በጣም የሚገርመው ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትን ከለቀቅሁ በኋላ የሀገሬን ብሄራዊ መዝሙር የመዘመርም ሆነ ባንዲራ የመስቀል አጋጣሚ ገጥሞኝ አለማወቁ ነው። አስቤውም አላውቅም። ቢያንስ ለምን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዳልቀጠለ አላውቅም። በእርግጥ እንደማንኛውም የመንግስት ተቋም ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ወይም ባንዲራ ጠዋት ወጥቶ ማታ እንደሚወርድ አስታውሳለሁ። ብዙሃኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ማለትም ተማሪዎች ግን የስነስርዓቱ አካል አልነበርንም።
ምናልባትም የኢትዮጵያዊነት መንፈስን ማዳከሚያ አንዱ መንገድ ተደርጎ ሊሆን ይችላል። በተለይ ደግሞ ባለፉት ዓመታት መንግስትን ጭምር ያሳሰበው የዜጎች የሰንደቅ ዓላማ ወይም የባንድራ ስሜት መውረድና ዓመታዊ የባንድራ በዓላትን ሳስብ ጥርጣሪዬን ከፍ ያደርገዋል።
Related Read:ትዝብት : በአዲስ አበባ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አግልግሎቶችየሀገር ውስጥ ጉዞንና ጉብኝትን ማሳደግ ለኢትዮጵያ ህልውናም ወሳኝ ነውህዳሴ ከተማን መገንባት አሰኘኝ __ ከህዳሴ ግድብ ጎን
እውነት ለመናገር ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተኑ ሁነቶች ሲያጋጥሙኝ ከብሄራዊ መዝሙሩ ይልቅ የጋሽ ጥላሁን 'ኢትዮጵያ...' ዘፈን ነበር ወደ አንደበቴ የሚመጣው። ሳላስበው እኔም ሰለባ ሆኜ አገኘሁት።
ዛሬ ከአማኑዔል ጥጋቡ ጋር የእሱ ት/ቤት ውስጥ ተገኘሁ። ሌላ ጊዜ ጠዋት ከት/ቤቱ በር አስገብቸው ነበር የምመለሰው። እንዳጋጣሚ ሆኖ ት/ቤቱ ጋር ጉዳይ ስለነበረኝ ጉዳዬ እሰከሚፈጸም ድረስ በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ መቆየት ነበረብኝ። እዛው እንዳለሁ የተማሪወች መግቢያ ሰዓት ደርሶ ባንዲራ እየወጣ ብሄራዊ መዝሙር ይዘመር ጀመረ። ከእነሱ ጋር ቆሜ እየዘመርኩ ረጂም ዓመት ወደኋላ ተጓዝኩ። አሁን በአገራችን ካለው ወቅት ጋር እያሰላሰልኩ ለደቂቃዎች ስሚታዊ ሆንኩኝ። ባንዲራው ከወጣና መዝሙሩ ካለቀ በኋላም ሀሳቤ አላቆም ሲለኝ ይህንን መከተብ አስፈለገኝ።
እስኪ እራሳችሁን ጠይቁ። በምን አጋጣሚ ብሄራዊ መዝሙር ዘምራችኋል፤ ባንዲራስ ሲወጣና ሲወርድ የስነስርዓቱ አካል ነበራችሁ? ምን አልባት እንደ እኔ የሆናችሁ ትኖሩ ይሆን?
በጣም የሚደንቀኝና የሚያስቀናኝ የሌሎች ያደላቸው ሀገር ፖለቲከኞች የሀገራቸውንና የህዝባችውን ደህንነትና ጥቅም አስጠብቀው የሌሎች ሀገሮች ጓዳ ዘልቀው ለእነሱ የሚሆናችውን ሲያሳድዱ እያየሁ የእኛዎቹ ብሽቆች እዚሁ እርስ በእርሳቸው ሲጠላለፉ እንደሚኖሩ ስታዘብ ምን አልባት የባንዲራ ስሜት ስለሌላቸው ይሆን እላለሁ።
Related Read:Aligning Ethiopian Energy Markets for Innovation and More JobsMy advise to Ethiopian Youth (Probably My Younger Self)- Live for a of Your Precious TimeLook Around- Wisdom is Under the Surface
ለዚህ ደግሞ ጥብቅ የሆነ የባንዲራ ስሜት ያላቸውን ወታደሮቻችን ሳይ ምልከታየን የበለጠ ያጎላዋል። ብሽቆች ፖለቲከኞች ያወሳሰቡትን ሳይቀር ውድ ሂወታቸውን ገብረው ለማስተካከል እዚህም እዚያም ሲባክኑ ሳይ በእነሱና በሌላው ማህበረሰብ ያለው ልዩነት የባንድራው ክብር እንደሆነ ይሰማኛል። የሌላው ማህበረሰብ የባንዲራ ስሜት ደግሞ በጊዜ ብዛት ሆን ተብሎ እንዲላላ የተሰራበት እንደሆነ አምናለሁ።
ያለን እርሾ ሳይጠፋ ቢታሰብበት እላለሁ። ተስፋ እንዳለንም የባለፉት ጥቂት ሳምንታት ምስክሮች ናቸው። ደግሞ ተረኛ ብሽቆች ያልተፈለገ መስመር ከማስያዛቸው በፊት።
መልካም።
One final Thought: What ever you do to succeed
Showing Up ^ Exposure Matters : It Is the First Key Step Leading You Where You Want to Go
Be bold to embrace It!
Do Subscribe to Showing Up ^ Exposure Matters to Receive Updates by Email
Comments