የአሁኑስ?
በእኔ እምነት የዘንድሮው ምርጫ ደግሞ ያለ ወቅቱ የመጣና አስፈሪ ገጽታ ያዘለ ነው። እኔ ስልጣን ቢኖረኝ እንዳይኖር የምፈልገው ዓይነት ምርጫ ነው። ለነገሩ ምርጫ በአጠቃላይ ባይኖሩ ወይም ባይፈጠሩ ከምመኛቸው ወሳኝ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ካመንኩኝ ቆይቻለሁ። ምን ይደረጋል። አንዴ ተፈጥሯልና አብረን ልንኖር ግድ ይላል። በሌላው አለምም ቢሆን በምርጫ ምክንያት ስልጣን በፍጹም የማይገባቸው ግለሰቦችን እንዳየን የሩቅ ጊዜ ትዝታ አይደለም። በየክልሎቹ የሚደረገው መፈናቀል ከምርጫ ጋር የተያያዘ ቢሆንስ። ከህዳሴ ባሻገር የሆነ ሃይል እንደዚህ እንዲሆን ፈልጎ ቢሆንስ። ፖለቲካችን እንደሁ በተንኮል የተሞላ ነው። ለዛም ነው ከአወንታዊ መገለጫዎቹ ይልቅ አሉታዊ ገጾቹ ጎልተው የሚታዩኝ።
በእርግጥ በአሁኗ ኢትዮጵያ መምረጥም ይሁን አለመምረጥ ለነጋችን ዋስትና የለውም። ሆኖም ግን በሌሎች ምርጫ ከሚወሰንብን መርጠን የሚመጣውን መጋፈጥ የሚሻል ይመስለኛል። ቢያንስ ሌሎችን ከምንወቅስ መርጠን ያሰብነው ባይሆን እንኳን ምርጫውን እንወቅሳለን።
እናም ጊዜው ሳያልፍ የምርጫ ካርድ አውጡ። ምን አልባት ወደመጨረሳው ቀልባችን የሚስብ ነገር እናገኝ ይሆናል። በዚህ ወሳኝ ወቅት
ከመምረጥ መመረጥ
ካለመምረጥ መምረጥ
ሳይሻል አይቀርም። እናም ጊዜው ሳያልፍ ካርድ እንድትወስዱ እመክራለሁ። በተለይ ደግሞ ለአቅመ ምርጫ የደረሳችሁ ወጣቶች ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት
በዚህ ምርጫ እኔ በግሌ ፓርቲዎችን ሳይሆን ግለሰቦችን መምረጥ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ፓርቲወች ውስጥ ብዙ ግብስብስ ሞልቷል። መልካም የሚባሉ ግለሰቦች ግን በሁሉም ፓርቲወች ውስጥ በአናሳ ቁጥር እንድሚገኙ አስባለሁ። እነዚህ በራሳቸው የቆሙ መልካም ግለሰቦች የህዝብን ይሁንታ ቢያገኙ ከፓርቲ ባሻገር እኛንም ሀገራቸውንም በአግባቡ ሊያገለግሉ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። የምርጫ መመሪያው የሚፈቅድ ከሆነ ቢያንስ አንድ ተወካይ ያለበት ሄጄ እመርጣለሁ።
በዚህ ምርጫ ምን ተስፋ አደርጋለሁ፡
እንደማንኛውም ሀገር ገዢ ፓርቲ የእኛውም
ገዢ ፓርቲ በተግባር የተፈተነ ውዝፍ እዳ አለበት። ውዝፍ እዳው የሚቀልለት ምናልባት ተቃዋሚ ሆኖ ከመጣ ብቻ ይመስለኛል። የትናንቱንና
ዛሬ እየሆነ ያለውን የሚያስረሳለትና የሚያካክስለት ከየት እንደሚያገኝ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። እስካሁን ከኖርንበትና ከምናውቀው
መንገድ በተለየ ለነገ ተስፋ የሚሰጠን አማራጭ ሃሳቦችን ( ተግባራዊ የሚሆኑ) መስማት የምቋምጥበት ወቅት ላይ ነኝ ።
ተፎካካሪዎች ደግሞ እንደ አሁን ቀደሙ ሁሉ እኛ
የምናውቀውንና የኖርንበትን የገዢ ፓርቲ ታሪክ ለእኛው በድጋሚ ከምታስታውሱን
በችግሩ ጥልቀት ልክ አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ የሚያወጣንን አማራች መንገድ እንድታመላክቱኝ ምኞቴ ነው። ከአሉባልታ በዘለለና
ሳይንሳዊ በሆኖ አመክንዮ የእያንዳንዳችሁ ሀሳብ ከሌሎቻችሁ የሚሻልበትን መንገድ ብታመላክቱኝ ቢቻል ቀልቤን ትስቡታላችሁ ካልሆነም
የተቀናቃኛችሁን ሃሳብ በቅጡ እንድረዳው ታግዙኛላችሁ።
በእኛ ሀገር ብዙ ጊዜ እንደህዝብም ሆነ እንደ ፓርቲ
ትኩረት የማንሰጠው ጉዳይ በገዢው ፓርቲ ድክመቶችና ስህተቶች ውስጥ ደረጃው ቢለያይም የሁላችንም ድርሻ እንዳለበት ነው። የህዝቡ
የዋህነት እንዲሁም የፖለቲካ ኢሊቶች ግትርነት እንደ ሀገር ለገባንበት ውጥንቅጥ አንድ አካል ብቻ ላይ መወርወር አሁንም የመፍትሄ
አቅጣቻው ላይ እንዳናታኩር ከመጋረድ ውጭ ብዙ የሚጠቅመው ነገር የሚኖረው አይመስለኝም። በአጭሩ አብሮኝ የሚያለቅስ ገዢ መደብ ሳይሆን ከችግሩ የምወጣበትን መንገድ የሚያመላክተኝ መሪ ፓርቲ ለማየት እጓጓለሁ። በዚህ ምርጫ።
በዚህ ምርጫ ከምንም በላይ ኮረጆ ከመገልበጥ እኩል የሚያሳስበኝ ሁሉም የፖለቲካ ሰዎች በሚባል ደረጃ እኔ በሰማሁትና በገባኝ ልክ መወሰን ሲገባኝ እናንታ የምትወስኑልን ነገር ነው። በዚህ ምርጫ ይሻሻላል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።
በ1997 ዓም ምርጫ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ።
እናማ በጊዜው የነበሩ ብልጣ ብልጦች እንድንመርጥ ካስጎመጁን በኋላ የቁርጡ ቀን ሲደርስ የምርጫ ወረቀት አለቀ ብለው ቅስማችን ሰብረውት
ነበር። በዚያም የተነሳ ለአላስፈላጊ ተቃውሞና መስዋእትነት ዳረጉን።
በዚያ ፍትጊያ ውስጥ ምርጫው አልፎም ተቃዋሚዎች ሆየ የህዝቡን ድምጽ ሜዳ በትነው የምርጫወን ነገር ዋጋ አሳጥተውት ነበር። ያኔ
የተሰበረው የምርጫ መንፈስ ያው እስከ አሁንም ድረስ አልተጠገነም።
ሌላው ስጋቴ ግትርነታችን ነው። በምርጫው ሂደትም
ይሁን ከውጤቱ ማግስት ለሀገር ጦስ የሚሆን ብዙ ፋወል የምንሰራው ነገር ያሰጋኛል። እርስ በእርሳችን መታገል መነጋገርና መግባባት
ሲገባን አንዱ በሌላው ላይ ነጥብ በማስቆጠር ስሌት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች
ሲሳይ የመሆናችን ነገር ከአሁኑ ሊታሰብበት ሊታረም የሚገባ አስተሳሰብ ይመስለኛል። ሶስተኛ ወገኖች አጋጣሚውን ተጠቅመው የራሳቸውን
ፍላጎትና ጥቅም ከማራመድ ባለፈ በየትኛውም አግባብ ለኢትዮጵያ የሚሆን ነገር ሲያደርጉ አላየሁም። ለኢትዮጵያ ያለናት እስከ ድክመታችንም
ቢሆን ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን። መሆን ያለበትም እሱ ነው። ተፎካካሪዎች መግባባት ቢያቅታቸው እንኳን በሃገር ውስጥ ከህዝባቸው ጋር
ሆነው መፍትሄውን እንደሚፈልጉ ተስፋየ ነው። ለዚህ ተገዥ የሆነም ከተጨማሪ ሃሳቦቹ ጋር የእኔን ምርጫ ያገኛል። እኛ ተኝተን የአባቶቻችን
ገድል ሳይቀር ደምስሠውና አዲስ ታሪክ ፈጥረው እያባሉን ከውጭ ወገኖች መልካም ነገር መጠበቅ ለእኔ ሞኝነት ነው የሚሆነው።
እስከ አሁን ከማውቃቸው ሀገራዊ ምርጫዎች የተማርኩት
የውጭ ሃይሎች ለተደረጉት ምርጫወች ከተደረጉ በኋላ እውቅና መንፈግን ነበር። በሚገርም ሁኔታ እኔም ድርጊታቸውን በከፊልም ቢሆን
እስማማበትና የእውነትም ይመስለኝ ነበር። አሁን የምታዘበው ግን በፍጹም ተቃራኒውን ነው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የውጭ ሃይሎች
ፊትለፊት ጥርሳቸውን እያሳዩ ተግባራቸው ግን ምርጫው የሚሰናከልበትን መንገድ እያሰመሩ እንዳሉ እየታዘብኩኝ ነው። የምርጫውን አካሄድ
ታዝበው ቅቡልነት ያለው ምርጫና መንግስት እንዳይኖረን ለማድረግ ሲረባረቡ እየታዘብኩኝ ነው ያለሁት። እስኪ ሌላውን ተውትና
ከአሁን ቀደም ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ የምርጫውን ሂደት በገንዘብም
ይሁን በሌላ መንገድ የሚደግፉትን ሀገሮች ፈልጓቸው። ብታምኑም ባታምኑም
በዚህ ምርጫ ለመምረጥ የወሰንኩት በዋናነት በዚህ ምክንያት ነው።
እኔ ምርጫን የማየው አንድ የፖለቲካ ፓርቲ በህዝብ
ቅቡልነት ባለው መንገድ ሃሳቡን ሸጦ ከምርጫ በኋላ ከህዝብ በተሰጠው ውክልና መሰረት መንግስታዊ መዋቅር ይዞ ሀገር ለመምራትና በተግባር
ለመፈተን ዝግጁ የሆነ እንደሆነ ነው። የምርጫ ሂደቱም ፖለቲካዊ ሃሳቡም
ከምርጫ በኋል ያለው ክስተትም ለህዝብ ቅቡልነቱ ወሳኞች ናቸው። ሁሉም ተፎካካሪዎች በዚህ ደረጀ ተስፋ እንድጥልባቸው ሆነው እንዲገኙ
ምኞቴ ነው። ሰላማችን፤ኢኮኖሚያችን፡የወጣቶች እጣ ፈንታ፤የውጭ ፖሊሲያችን፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተግባቦቶቻችን በቀሩት ጊዜቶች በቅርበት
ለመስማት ዝግጁ የሆንኩበት ወቅት ላይ ነኝ። ለመወስን እንዲመቸኝ።
ለአሁኑ ግን ጊዜው ሳያልፍ የምርጫ ካርድ ውሰዱ። ከዛም የሚሆነውን አብረን እናያለን።
Showing Up ^ Exposure Matters!! It Is the First Key Step Leading You Where You Want to Go
Be bold to embrace It!
Comments