ለውጥ ምን ያህል ከባድ እንደሆነና ምን ያህልም ቁርጠኝነት ጊዜ ትግስትና ግብዓት እንደሚፈልግ የአሁኑ የሀገራችን ሁኔታ ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። ከሁሉ በላይ ያለ በቂና አሳማኝ ምክንያት ብዙዎች የሂወት መስዋእትነት ከፈሉ። ብዙዎቻችንንም አሳዘነ። ይሁን እንጂ በዚህ መጠን መስዋእትነት የተከፈለበት ሃገራዊ ለውጥ በምንም መልኩ መስመሩን እንዳይስት መጠንቀቅ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። አንድም ተጨማሪ መስዋእት እንዳንከፍል ሁለትም የተከፈለው መስዋእትነት ለወደፊት ትምህርት በሚሆነን መልኩ ለውጡን ማስቀጠልና ግቡን መምታት የግድ ነው። ads Any Plan to Travel to Ethiopia , Book with Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia አንዳንድ ወገኖች እየሆነ ባለው አስከፊ ክስተት ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ ይታይባቸዋል። መሪዎችም ጭምር እንዲህ ካልሆነ ስልጣኔን እለቃለሁ እንዲያ ካልሆነ ከእነእንትና ጋር መስራት ያስቸግረኛል ሲሉ ይደመጣሉ። ስልጣን ከለቀቅህማ ፎርፌ ሆነ ማለት ነው። የሴራ ፖለቲካ በነገሰበትና ብቁ ተቋም ባልተገነባበት ሁኔታ ከትግሉ በራስህ ፈቃድ ወጣህ ማለት ለውጡ ወደማትፈልገው መስመር በነጻነት እንዲጓዝ ፈቀድህ ማለት ነው። ባይሆን ቦታውን ካንተ/ካንቺ በተሻለ ሊታገል የሚችል ሰው ተክተህ/ተክተሽ የራስህን/የራስሽን ቦታ መፈለግ ብልህነት ነው። እኔ አሁን ኢትዮጵያ ለገባችበት ቅርቃር አንዱ ምክንያት ከዓመታት በፊት በነበረው ተመሳሳይ የለውጥ ወቅት በጊዜው የነበሩ ሰዎች በተለይ ደግሞ ባለስልጣናትና ሹመኞች የወቅቱን ሴረኛ ቡድን በተሻለ ሃሳብ መታገልና መመከት ያለመቻላቸው ውጤት እንደሆነ ነው የማስበው። ግማሾቹ ሃሳቡ ሳይስማማቸው ሲቀር እየወጡ ቀሪወቹ ደግሞ በተናጠል
It is the 1st key step leading you where you want to go!