Skip to main content

Posts

Showing posts from 2020

የሀገር ሰንደቅ ዓላማና የብሄራዊ መዝሙር ስሜት ጉዳይ

              የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ  ጊዜ ተጓዥ ነው። እድሜም እንዲሁ።  አሁን ላይ ድሮ በሚባል ደረጃ  የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያለን  በት/ቤታችን  የሀገራችን  ብሄራዊ  መዝሙር  ከልብ  እንዘምር ነበር።   የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ እንደ እኔ ልጅ  ( እንደተንኮለኞች ደግሞ አጭር)   ስለነበርኩ  ከፊት ስለምሰለፍ  ብዙ ጊዜ ባንድራ የመስቀል እድል ነበረኝ። አለማየሁ ( ሌላኛው አጭር ) ካልቀደመኝ በስተቀር። ባንዲራ ሲወጣና ሲወርድ ልክ እንደ ቅዳሴ መጀመሪያ ሁሉም ባለበት ነበር የሚቆመው።     በጣም የሚገርመው ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤትን ከለቀቅሁ በኋላ   የሀገሬን ብሄራዊ መዝሙር የመዘመርም ሆነ ባንዲራ የመስቀል አጋጣሚ ገጥሞኝ አለማወቁ ነው። አስቤውም አላውቅም። ቢያንስ ለምን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዳልቀጠለ አላውቅም። በእርግጥ እንደማንኛውም የመንግስት ተቋም ብሄራዊ  ሰንደቅ ዓላማ ወይም  ባንዲራ ጠዋት ወጥቶ ማታ እንደሚወርድ አስታውሳለሁ። ብዙሃኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ማለትም ተማሪዎች ግን የስነስርዓቱ አካል አልነበርንም።    ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  ምናልባትም የኢትዮጵያዊነት መንፈስን ማዳከሚያ አንዱ መንገድ ተደርጎ ሊሆን ይችላል። በተለይ ደግሞ ባለፉት ዓመታት መንግስትን ጭምር ያሳሰበው የዜጎች  የሰንደቅ ዓላማ ወይም  የባንድራ ስሜት መውረድና  ዓ መታዊ የባንድራ በዓላትን ሳስብ ጥርጣሪዬን ከፍ ያደርገዋል።   Related R

ትዝብት : በአዲስ አበባ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አግልግሎቶች

      አዲስ አበባ  ከተማ ብዙውን ህዝብ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው ወይም የሚያስተሳስረው ቀበሌ ከፍ ሲልም ክ / ከተማ ውስጥ ያሉ ክንውኖችና አገልግሎቶች ናቸው ቢባል የተጋነነ አይመስለኝም። ብዙ ሀዝብ በውስጧ እንደመያዟ በከተማችን ውስጥ በሚገኙ ቀበሌወችና ክ / ከተሞች የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶችም እንዲሁ የበዙ ናቸው።   በጊዜ ካየነው የአሁኑ የአገለግሎቶት አሰጣጥ ከድሮው ጥሩ የሚባል መሻሻል ይታይበታል። መሆን ካለበት አንጻር ግን አሁንም በእጅጉ መፈተሽና መሻሻል የሚገባቸው ናቸው።    ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  በቅርቡ በአንዱ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ተገኝቼ የታዘብኩትን ምን አልባት ከጠቀመና የቀበሌና የክፍለ ከተማ ሰወች ካሰቡበት በሚል እንደሚከተለው ላካፍላችሁ። 30 ደቂቃ የማይውስድ ጉዳይ ሙሉቀን እዛው ውዬ ለዚያውም ወደሚቀትለው ቀን ሊያሻግሩት ሞክረው የትዕግቴ ጉዳይ ገርሟቸው ከስራ መውጫ ሰዓት ዘግይተው ነው ጉዳዬን የጨረሱልኝ። ምንም እንኳን እንደተገልጋይ የሚያበሳጭ ቢሆንም ምንም እንደማላመጣ ተረድቼ ከስሜት በጸዳ መልኩ ያሉትን ክፍተቶች ለመታዘብ ሞክሬያለሁ።      ሶስት አበይት ጉዳዮችን ታዝቤአለሁ።   ስራ የሚሰሩበት ሲስተም ረጅም ጊዜ የሚወስድና የሚቆራረጥ መሆኑን  ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ ቦታወች ላይ የተመደቡት ተመሳሳይ ቋንቋ የሚችሉ ( ብሄር  ለማለት    የሚያስደፍር   መረጃ