ብዙውን ህዝብ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው ወይም የሚያስተሳስረው ቀበሌ ከፍ ሲልም ክ/ከተማ ውስጥ ያሉ ክንውኖችና አገልግሎቶች ናቸው ቢባል የተጋነነ አይመስለኝም። ብዙ ሀዝብ በውስጧ እንደመያዟ በከተማችን ውስጥ በሚገኙ ቀበሌወችና ክ/ከተሞች የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶችም እንዲሁ የበዙ ናቸው።
በጊዜ ካየነው የአሁኑ የአገለግሎቶት አሰጣጥ ከድሮው ጥሩ የሚባል መሻሻል ይታይበታል። መሆን ካለበት አንጻር ግን አሁንም በእጅጉ መፈተሽና መሻሻል የሚገባቸው ናቸው።
በቅርቡ በአንዱ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ተገኝቼ የታዘብኩትን ምን አልባት ከጠቀመና የቀበሌና የክፍለ ከተማ ሰወች ካሰቡበት በሚል እንደሚከተለው ላካፍላችሁ። 30 ደቂቃ የማይውስድ ጉዳይ ሙሉቀን እዛው ውዬ ለዚያውም ወደሚቀትለው ቀን ሊያሻግሩት ሞክረው የትዕግቴ ጉዳይ ገርሟቸው ከስራ መውጫ ሰዓት ዘግይተው ነው ጉዳዬን የጨረሱልኝ። ምንም እንኳን እንደተገልጋይ የሚያበሳጭ ቢሆንም ምንም እንደማላመጣ ተረድቼ ከስሜት በጸዳ መልኩ ያሉትን ክፍተቶች ለመታዘብ ሞክሬያለሁ።
ሶስት አበይት ጉዳዮችን ታዝቤአለሁ።
- ስራ የሚሰሩበት ሲስተም ረጅም ጊዜ የሚወስድና የሚቆራረጥ መሆኑን
- ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ ቦታወች ላይ የተመደቡት ተመሳሳይ ቋንቋ የሚችሉ(ብሄር ለማለት የሚያስደፍር መረጃ የለኝም) መሆኑ
- አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች በተጨናነቀ ሁኔታ የሚሰሩ መሆኑ ናቸው።
የተዘረጋው የአይቲ ኢንፍራስትራክቸርና ሲስተም አስተማማኝና ተገቢው ፍጥነት የለውም። ምክንያቱ ብዙ ሊሆን ይችላል። ተገልጋዩ አገልግሎት የሚሰጠው ሰራተኛ ሆን ብሎ የሚያዘገየውና ሲስተሙ ተቋረጠ እንደሚል ነው የሚረዳው። ከአሁን በፊት ሌላ የመንግስት ተቋም ውስጥ እኔም ተመሳሳይ ነገር ገጥሞኝ ያውቃል። አይደረግም ባልልም እዚህ ግን እንደዚያ አይደለም የተረዳሁት። ኮምፒውተር ከመሆኑ በስተቀር ሁሉም መረጃ የሚገባው ከማኑዋል ባነሰ ፍጥነት ነው። ሲስተም ለመባል ብቁ አይደለም። ሰራተኞችም በቂ ክህሎት እንዲኖራቸው አልተደረገም።
Related Read:
የሀገር ውስጥ ጉዞንና ጉብኝትን ማሳደግ ለኢትዮጵያ ህልውናም ወሳኝ ነውህዳሴ ከተማን መገንባት አሰኘኝ __ ከህዳሴ ግድብ ጎን
ዋናው የከተማው አገልግሎት የሚሰጠው እነዚህ ቦታወች ላይ ሆኖ እያለ ተገቢው ኢንፍራስትራክቸርና የሰው ሃይል ልማት ትኩረት ያገኘ አልመሰለኝም። በዚህም ምክንያት ተገልጋዩ ሲማረር አገልግሎት ሰጪውን ደግሞ ምስጋናቢስ ያደርጋል። ይህንንም ነው የታዘብኩት።
2. ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ ቦታወች ላይ የተመደቡት አግልግሎት ሰጪወች ተመሳሳይ ቋንቋ የሚችሉ( ብሄር ለማለት የሚያስደፍር መረጃ የለኝም) መሆኑ
ሁሉም በሚባል ደረጃ ስራ ፈላጊወችና ትሁት ወጣቶች ናቸው። እነሱ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ወይም ሌላ ሰው ሆን ብሎ አስቀምጧቸው ወሳኝ የሆኑ ቦታወች ላይ የተቀመጡት ወጣቶች ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገሩ ነበሩ። ቀበሌው መሃል ከተማ ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ አጋጣሚ እንደማይሆን ማናችንም የምንረዳው ጉዳይ ነው። ተመሳሳይ ቋንቋ መናገራቸው አይደለም ጉዳዩ። ይልቅስ ተመሳሳይና የተጠና ስነልቦና ያላቸው መሆኑ ነው።
አገልግሎት አሰጣጡ ዘገምተኛ ሰለነበር በጣም ብዙ ተገልጋዮች ነበሩ። ወረፋውም እንደዚሁ። ከእነሱ ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገር ተገልጋይ ሲመጣ ከተገልጋዩ ጋረ የተቀላቀሉ ጉዳይ አስፈጻሚዎች ጋር ይነጋገሩና ወደ ውጭ እንዲሄዱ ይደረጋሉ። ጉዳይ አስፈጻሚወቹ መረጃውን ከተገልጋዩ ይቀበሉና በውስጥ በኩል ያስተላልፉታል። ተገልጋዮችም ያለወረፋቸው ተስተናግደው ይሄዳሉ። ወረፋውን የሚጠብቀው አያውቅም። የለየለት ሙስና አይታያችሁም። ለዚህ ምቹ ሁኔታ የፈጠረው ደግሞ አግልግሎት ሰጪወቹ ተስተካክለው መቀመጣቸው ነው። አንዳቸው አንዳቸውን አያደናቅፉም። አጋጣሚው ሲመቻቸው ሁላቸውም እንደሚያደርጉት ነው የማስበው።
Related Read:
እንደነሱ ተመሳሳይ ቋንቋ የሚችል ተገልጋይ በዚህ መልኩ ቀርበውት ሳይስማማ ቀርቶ ሲበሳጭ ሳየው ቀርቤ አናገርኩት። መጀመሪያ የነበረኝን ጥርጣሬም የበለጠ አጎላልኝ።
ሙስናና አላስፈላጊ ቢሮክራሲ ክፉወች ናቸው። የብዙ ወጣቶችን ተስፋ ያመክናሉ። የሁላችንም ሀገር ተስፋ ያጨልማሉ። በቅርብ ጊዜ ያየነው ይሄን ነው። ለውጥ ካልን አይቀር የምር መለወጥ ይኖርብናል። ከተማ አስተዳደሩም ይሁን መንግስት ተገቢውን ክፍያ ከፍሎ(ገንዘቡ መውጣቱ ላይቀር) ከዚያ ሲዘል ተጠያቂነትን ማስፈን ይኖርበታል።
ኮንደሙኔምን ያህክል ነገር ያላግባብ እንደሚሆን ካደረጉ በኋላ ለገበሬ እንደማናስብ የሚያስጮሁት አይነት ሁለተኛ ጉዳት የትም አያደርሰንም። ከአሁኑ ቢታሰብበት እላለሁ።
3. አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች በተጨናነቀ ሁኔታ የሚሰሩ መሆኑ
ኮሮናንማ አታስቡት። አገልግሎት ሰጪውም ተገልጋዩም በጣም በተጨናነቀ ሁኔታ ነው ስራ ሲሰራ የታዘብኩት። በእርግጥ ማስክ አለ።
ሌላው የታዘብኩት ተገልጋዩ ከመብዛቱና ሲስተሙ ዘገምተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሰራተኞች ለረጂም ሰዐት ለዚያዉም የሚበሳጭ አንዳንዴም የሚሳደብ ደምበኛ እያስተናገዱ መዋላቸውን ነው። ሻይ ይቅርና ለምሳም ለመውጣት በግብግብ ነው። ተስተናጋጁ በፍጹም አይራራላቸውም። ተመሳሳይ ነገር በክፍለ ከተማ ገቢወችም ከአንድ አመት በፊት በሌላ አጋጣሚ ታዝቤ ነበር።
Related Read: Look Around- Wisdom is Under the Surface
ይሄ ለጤናም፣ ለስነልቦናም ለስራ ፍቅርም ጥሩ ሆኖ አላገኘሁትም። የሚያስተባብር ሰውም አላየሁም። ሁሉም ደምበኛ ወይም ተስተናጋዥ እየገባ የሌላን ደምበኛ ጉዳይ የያዘውን አገልግሎት ሰጪ ነው እያቋረጠ የሚጠይቀው። ተስተናጋጁ ምን ጉዳይ የት ሄዶ እንደሚያስፈጽም ግልጽነት የለም። ስራ አስኪያጆች ወይም አስተባባሪዎች ክፍተት እያዩና ሰራ ሊያፋጥኑ የሚችሉ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ አላየሁም። በዚህም አገልግሎት ተጠቃሚዎች የበለጥ ሲማረሩ ነው የታዘብኩት።
ምንም እንኳን ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር ተጨማሪ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን ብረዳም አብዛሃኛውን ግን ባለበት ማስተካከል ይቻላል። ቅንነትና ነባራዊ ሁኔታወችን ተረድቶ ማስተካከያ ለመውሰድ መዘጋጀት ነው የሚጠይቀው። በደምብ ለማየት ስትሞክሩ ሆን ተብሎ በዝርክርክ ከባቢ እና በምሬት መካከል ለራስ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተደረገ ነው የሚመስለው። ይሄም ለጋራ ከተማችንም ይሁን ለሀገራችን ስለማይጠቅም ቢታሰብበት እላለሁ።
One final Thought: What ever you do to succeed
Showing Up ^ Exposure Matters : It Is the First Key Step Leading You Where You Want to Go
Be bold to embrace It!
Do Subscribe to Showing Up ^ Exposure Matters to Receive Updates by Email
Comments