Skip to main content

Posts

Showing posts with the label አዲስ አበባ፣ የቀበሌና ክ/ከተማ አገልግሎቶች፤

ትዝብት : በአዲስ አበባ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አግልግሎቶች

      አዲስ አበባ  ከተማ ብዙውን ህዝብ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው ወይም የሚያስተሳስረው ቀበሌ ከፍ ሲልም ክ / ከተማ ውስጥ ያሉ ክንውኖችና አገልግሎቶች ናቸው ቢባል የተጋነነ አይመስለኝም። ብዙ ሀዝብ በውስጧ እንደመያዟ በከተማችን ውስጥ በሚገኙ ቀበሌወችና ክ / ከተሞች የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶችም እንዲሁ የበዙ ናቸው።   በጊዜ ካየነው የአሁኑ የአገለግሎቶት አሰጣጥ ከድሮው ጥሩ የሚባል መሻሻል ይታይበታል። መሆን ካለበት አንጻር ግን አሁንም በእጅጉ መፈተሽና መሻሻል የሚገባቸው ናቸው።    ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  በቅርቡ በአንዱ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ተገኝቼ የታዘብኩትን ምን አልባት ከጠቀመና የቀበሌና የክፍለ ከተማ ሰወች ካሰቡበት በሚል እንደሚከተለው ላካፍላችሁ። 30 ደቂቃ የማይውስድ ጉዳይ ሙሉቀን እዛው ውዬ ለዚያውም ወደሚቀትለው ቀን ሊያሻግሩት ሞክረው የትዕግቴ ጉዳይ ገርሟቸው ከስራ መውጫ ሰዓት ዘግይተው ነው ጉዳዬን የጨረሱልኝ። ምንም እንኳን እንደተገልጋይ የሚያበሳጭ ቢሆንም ምንም እንደማላመጣ ተረድቼ ከስሜት በጸዳ መልኩ ያሉትን ክፍተቶች ለመታዘብ ሞክሬያለሁ።      ሶስት አበይት ጉዳዮችን ታዝቤአለሁ።   ስራ የሚሰሩበት ሲስተም ረጅም ጊዜ የሚወስድና የሚቆራረጥ መሆኑን...