Skip to main content

Posts

Showing posts with the label የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ፤ ብሄራዊ መዝሙር

የሀገር ሰንደቅ ዓላማና የብሄራዊ መዝሙር ስሜት ጉዳይ

              የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ  ጊዜ ተጓዥ ነው። እድሜም እንዲሁ።  አሁን ላይ ድሮ በሚባል ደረጃ  የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያለን  በት/ቤታችን  የሀገራችን  ብሄራዊ  መዝሙር  ከልብ  እንዘምር ነበር።   የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ እንደ እኔ ልጅ  ( እንደተንኮለኞች ደግሞ አጭር)   ስለነበርኩ  ከፊት ስለምሰለፍ  ብዙ ጊዜ ባንድራ የመስቀል እድል ነበረኝ። አለማየሁ ( ሌላኛው አጭር ) ካልቀደመኝ በስተቀር። ባንዲራ ሲወጣና ሲወርድ ልክ እንደ ቅዳሴ መጀመሪያ ሁሉም ባለበት ነበር የሚቆመው።     በጣም የሚገርመው ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤትን ከለቀቅሁ በኋላ   የሀገሬን ብሄራዊ መዝሙር የመዘመርም ሆነ ባንዲራ የመስቀል አጋጣሚ ገጥሞኝ አለማወቁ ነው። አስቤውም አላውቅም። ቢያንስ ለምን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዳልቀጠለ አላውቅም። በእርግጥ እንደማንኛውም የመንግስት ተቋም ብሄራዊ  ሰንደቅ ዓላማ ወይም  ባንዲራ ጠዋት ወጥቶ ማታ እንደሚወርድ አስታውሳለሁ። ብዙሃኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ማለትም ተማሪዎች ግን የስነስርዓቱ አካል አልነበርንም።    ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  ምናልባትም የኢትዮጵያዊነት መንፈስን ማዳከሚያ አንዱ መንገድ ተደርጎ ሊሆን ይችላል። በተለይ ደግሞ ባለፉት ዓመታት መንግስትን ጭምር ያሳሰበው የዜጎች  የሰንደቅ ዓላማ ወይም  የባንድራ ስሜት መውረድና  ዓ መታዊ የባንድራ በዓላትን ሳስብ ጥርጣሪዬን ከፍ ያደርገዋል።   Related R