ምክንያቱን ባላውቅም ብዙ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ከማየትና ከመጎብኘት ይልቅ ከቻሉ ወደ ውጭ መጓዝን ይወዳሉ። ለስደትም ቢሆን። የጉዞ መዳረሻዎችም ሳይቀሩ ከራሳቸው ዜጎች ይልቅ የውጭ ጎብኝዎችን ለማስተናገድ የተመቻቹ ናቸው። ከአማርኛ ከኦሮምኛ ከትግርኛ ወይም ከሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ይልቅ ብዙም ባልቀና እንግሊዘኛ ታሪክን ማስረዳት ይቀላቸዋል። ይህ የቅርብ ማለትም የሶስትና የአራት ዓመት ክስተት ብቻ አይደለም። በእርግጥ በቅርብ ጊዜ አገራችን ቀበሌ አቋርጦ ለመጓዝ አይደለም ለኗሪዎቿም ፈታኝ ሆናለች። በአውስቶቡስ ስትጓዙ ኪሳችሁን ለመዳበስ አለበለዚያም ማደሪያ አልጋ እንድትይዙ ሊያግባባችሁ ካልሆነ በቀር የአካባቢውን ታሪክ ሊያስረዳችሁ የሚሞክር እምብዛም ነው። ድሮም ቢሆን። ኢትዮጵያውያን አብሮ ለመኖር አገራቸውን በልኳ ማወቅ የግድ የሚላቸው ወቅት ላይ ናቸው። ምንአልባትም አሁን ላይ ያለው ግርግር ዜጎች አገራቸውን በልኳ ካለማወቃቸው የተነሳ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መሰረቱ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው በገጠሩ የሚኖረው ኩሩው ገበሬና አርብቶ አደር ማህበረሰብ ነው። ይህ የሀገሪቱ መሰረት የሆነው የገጠሩ ማህበረሰብ ደግሞ እምቅ የሆኑ ማህበራዊ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ነው። ያውም ጠንካራ የሆኑ። ይሁን እንጂ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የህዝባችን የእድሜ ስብጥር( ዲሞግራፊ) በእጅጉ እየተቀየረ እየሄደ ነው። ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የወጣቶች ሀገር እንደምትሆን እየተተነበየ ነው። ይህ ጥሩ እድል ቢሆንም ጥሩ ያልሆነ ነገር ይዞ መምጣቱም የማይቀር ነው። በቅጡ ካልተዘጋጀን በስተቀር። የትምህርት ጥራት ጉድለት ተጨምሮበት ወጣቱ ትውልድ ጠንካራ የነበረውን የአባቶቹን እሴቶች ይዞ ለመቀጠል ሲቸገር እየታዘብን ነው። በእ...
It is the 1st key step leading you where you want to go!