እኔ እራሴ ለአቅመ ምርጫ ከደረስኩ ወዲህ የ 1997 ዓ፣ም ምርጫ ቢያንስ በሂደቱ ለእውነት የተጠጋ ይመስለኛል። ከ 1997 ዓም ምርጫ ወዲህ የተካሄዱት ምርጫዎች በአንጻሩ ምርጫዎች ይሁኑ ቅርጫዎች እስካሁን ማረጋገጫ የተገኘላቸው አይመስለኝም። የአሁኑስ ? በእኔ እምነት የዘንድሮው ምርጫ ደግሞ ያለ ወቅቱ የመጣና አስፈሪ ገጽታ ያዘለ ነው ። እኔ ስልጣን ቢኖረኝ እንዳይኖር የምፈልገው ዓይነት ምርጫ ነው። ለነገሩ ምርጫ በአጠቃላይ ባይኖሩ ወይም ባይፈጠሩ ከምመኛቸው ወሳኝ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ካመንኩኝ ቆይቻለሁ። ምን ይደረጋል። አንዴ ተፈጥሯልና አብረን ልንኖር ግድ ይላል። በሌላው አለምም ቢሆን በምርጫ ምክንያት ስልጣን በፍጹም የማይገባቸው ግለሰቦችን እንዳየን የሩቅ ጊዜ ትዝታ አይደለም። በየክልሎቹ የሚደረገው መፈናቀል ከምርጫ ጋር የተያያዘ ቢሆንስ። ከህዳሴ ባሻገር የሆነ ሃይል እንደዚህ እንዲሆን ፈልጎ ቢሆንስ። ፖለቲካችን እንደሁ በተንኮል የተሞላ ነው። ለዛም ነው ከአወንታዊ መገለጫዎቹ ይልቅ አሉታዊ ገጾቹ ጎልተው የሚታዩኝ። በእርግጥ በአሁኗ ኢትዮጵያ መምረጥም ይሁን አለመምረጥ ለነጋችን ዋስትና የለውም። ሆኖም ግን በሌሎች ምርጫ ከሚወሰንብን መርጠን የሚመጣውን መጋፈጥ የሚሻል ይመስለኛል።...
It is the 1st key step leading you where you want to go!