Skip to main content

Posts

በለውጥ መንገድ ላይ ከያዙ አይለቁ!

  ለውጥ ምን ያህል ከባድ እንደሆነና ምን ያህልም ቁርጠኝነት ጊዜ ትግስትና ግብዓት እንደሚፈልግ የአሁኑ የሀገራችን ሁኔታ ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። ከሁሉ በላይ ያለ በቂና አሳማኝ ምክንያት ብዙዎች የሂወት መስዋእትነት ከፈሉ። ብዙዎቻችንንም አሳዘነ። ይሁን እንጂ በዚህ መጠን መስዋእትነት የተከፈለበት ሃገራዊ ለውጥ በምንም መልኩ መስመሩን እንዳይስት መጠንቀቅ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። አንድም ተጨማሪ መስዋእት እንዳንከፍል ሁለትም የተከፈለው መስዋእትነት ለወደፊት ትምህርት በሚሆነን መልኩ ለውጡን ማስቀጠልና ግቡን መምታት የግድ ነው።   ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  አንዳንድ ወገኖች እየሆነ ባለው አስከፊ ክስተት ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ ይታይባቸዋል። መሪዎችም ጭምር እንዲህ ካልሆነ ስልጣኔን እለቃለሁ እንዲያ ካልሆነ ከእነእንትና ጋር መስራት ያስቸግረኛል ሲሉ ይደመጣሉ። ስልጣን ከለቀቅህማ ፎርፌ ሆነ ማለት ነው። የሴራ ፖለቲካ በነገሰበትና ብቁ ተቋም ባልተገነባበት ሁኔታ ከትግሉ በራስህ ፈቃድ ወጣህ ማለት ለውጡ ወደማትፈልገው መስመር በነጻነት እንዲጓዝ ፈቀድህ ማለት ነው። ባይሆን ቦታውን ካንተ/ካንቺ በተሻለ ሊታገል የሚችል ሰው ተክተህ/ተክተሽ የራስህን/የራስሽን ቦታ መፈለግ ብልህነት ነው።   እኔ አሁን ኢትዮጵያ ለገባችበት ቅርቃር አንዱ ምክንያት ከዓመታት በፊት በነበረው ተመሳሳይ የለውጥ ወቅት በጊዜው የነበሩ ሰዎች በተለይ ደግሞ ባለስልጣናትና ሹመኞች የወቅቱን ሴረኛ ቡድን በተሻለ ሃሳብ መታገልና መመከት ያለመቻላቸው ውጤት እንደሆነ ነው...

Get Out of Your Comfort Zone

I find this write up on Linkedin( by Stéphane Hervout  ) and wanted to share it here to serve further inspiration.   Have you ever heard of the saying "Life starts outside of your comfort zone"?. The visual below represents how breaking out of your comfort zone can be a step towards achieving things you never thought were possible. The four stages in this diagram include: 1️⃣   Comfort Zone : The majority of people are happy to be in the 'Comfort Zone' where they feel safe and in control of their situation. You may have perfected a daily routine or become comfortable in your job role. 2️⃣  Fear Zone : you will reach an unknown zone. To reach this zone of fear and evolve successfully, you must learn to see failure as a stepping stone to success. In the fear zone, you will probably lack self-confidence. The opinions of others may affect you. 3️⃣  Learning Zone :Your passage through this new and unknown zone of fear can last for some time. You will persever...

የሀገር ሰንደቅ ዓላማና የብሄራዊ መዝሙር ስሜት ጉዳይ

              የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ  ጊዜ ተጓዥ ነው። እድሜም እንዲሁ።  አሁን ላይ ድሮ በሚባል ደረጃ  የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያለን  በት/ቤታችን  የሀገራችን  ብሄራዊ  መዝሙር  ከልብ  እንዘምር ነበር።   የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ እንደ እኔ ልጅ  ( እንደተንኮለኞች ደግሞ አጭር)   ስለነበርኩ  ከፊት ስለምሰለፍ  ብዙ ጊዜ ባንድራ የመስቀል እድል ነበረኝ። አለማየሁ ( ሌላኛው አጭር ) ካልቀደመኝ በስተቀር። ባንዲራ ሲወጣና ሲወርድ ልክ እንደ ቅዳሴ መጀመሪያ ሁሉም ባለበት ነበር የሚቆመው።     በጣም የሚገርመው ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤትን ከለቀቅሁ በኋላ   የሀገሬን ብሄራዊ መዝሙር የመዘመርም ሆነ ባንዲራ የመስቀል አጋጣሚ ገጥሞኝ አለማወቁ ነው። አስቤውም አላውቅም። ቢያንስ ለምን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዳልቀጠለ አላውቅም። በእርግጥ እንደማንኛውም የመንግስት ተቋም ብሄራዊ  ሰንደቅ ዓላማ ወይም  ባንዲራ ጠዋት ወጥቶ ማታ እንደሚወርድ አስታውሳለሁ። ብዙሃኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ማለትም ተማሪዎች ግን የስነስርዓቱ አካል አልነበርንም።    ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  ምናልባትም የኢትዮጵያዊነት መንፈስን ማዳከሚያ ...

ትዝብት : በአዲስ አበባ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አግልግሎቶች

      አዲስ አበባ  ከተማ ብዙውን ህዝብ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው ወይም የሚያስተሳስረው ቀበሌ ከፍ ሲልም ክ / ከተማ ውስጥ ያሉ ክንውኖችና አገልግሎቶች ናቸው ቢባል የተጋነነ አይመስለኝም። ብዙ ሀዝብ በውስጧ እንደመያዟ በከተማችን ውስጥ በሚገኙ ቀበሌወችና ክ / ከተሞች የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶችም እንዲሁ የበዙ ናቸው።   በጊዜ ካየነው የአሁኑ የአገለግሎቶት አሰጣጥ ከድሮው ጥሩ የሚባል መሻሻል ይታይበታል። መሆን ካለበት አንጻር ግን አሁንም በእጅጉ መፈተሽና መሻሻል የሚገባቸው ናቸው።    ads  Any Plan to Travel to Ethiopia ,  Book    with  Afro Experience Your Travel Guide in Ethiopia  በቅርቡ በአንዱ ቀበሌና ክፍለ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ተገኝቼ የታዘብኩትን ምን አልባት ከጠቀመና የቀበሌና የክፍለ ከተማ ሰወች ካሰቡበት በሚል እንደሚከተለው ላካፍላችሁ። 30 ደቂቃ የማይውስድ ጉዳይ ሙሉቀን እዛው ውዬ ለዚያውም ወደሚቀትለው ቀን ሊያሻግሩት ሞክረው የትዕግቴ ጉዳይ ገርሟቸው ከስራ መውጫ ሰዓት ዘግይተው ነው ጉዳዬን የጨረሱልኝ። ምንም እንኳን እንደተገልጋይ የሚያበሳጭ ቢሆንም ምንም እንደማላመጣ ተረድቼ ከስሜት በጸዳ መልኩ ያሉትን ክፍተቶች ለመታዘብ ሞክሬያለሁ።      ሶስት አበይት ጉዳዮችን ታዝቤአለሁ።   ስራ የሚሰሩበት ሲስተም ረጅም ጊዜ የሚወስድና የሚቆራረጥ መሆኑን...